የአዲስ ኪዳን ክብር ከብሉይ ኪዳን ክብር ይልቃል

በ2ኛ ቆሮንቶስ ም 3: 7-18 ጳውሎስ የአዲስ ኪዳን ክብር ከብሉይ ኪዳን ክብር ይልቃል ብሎ ይጀምራል። ምክንያቱም ብሉይ ኪዳን ለተወሰነ ጊዜ እና ሊሻር የተጀመረ ስለነበረ ነውና። ደግሞ ወደ ሞት አቅጣጫ የሚመራ አገልግሎት ነው። የፍርድና የኩነኔ አገልግሎትም ነበር። እንደገና በፊደላት በድንጋይ ላይ የተቀረጸ ነበርና። 

የእሥራኤል ልጆች የፊተኛው ኪዳን ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ አከበሩት።  አሁን ግን የጽድቅ አገልግሎት ያለው ጸንቶም የሚኖር አዲስ ኪዳን ተሰጠ።  ታዲያ ያ ይሻር የነበረ ኪዳን እንደዛ ከተከበረ እንዴት ጸንቶ የሚዘልቀው አዲሱ ኪዳን ይልቅ ክብር አይሰጠውም?  “እኔ ደግሞ ሙሴ የሚሻረውን ክብር የእስራኤል ልጆች ትኩር ብለው እንዳይመለከቱት በመጋረጃ እንደሸፈነው ሳይሆን በአዲሱ ኪዳን ካለን ተስፋ የተነሣ ገልጠነው እንናገራለን” ይላቸዋል።  መጋረጃው በክርስቶስ ብቻ የሚሻር ስለሆነ ዛሬም ብሉይ ኪዳን ሲነበብ መጋረጃው በልባቸው አለ። ግን ወደ ጌታ ዞሮ ባሉ ጊዜ መጋረጃው ይወስዳል ብሎ በጌታ መንፈስ የሚሆነውን ደህንነት ያመላክታቸዋል። 

Flower with Green Background

 

ጌታ መንፈስ ነው። የጌታ መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። እኛም ጌታን እያንጸባረቅን ደረጃ በደረጃ ወደ እርሱ ክብር እንለወጣለን ይላቸዋል።